አገልግሎቶች እና ዋጋ
እንደ ፍላጎትዎ የሚበጁ ሙያዊ አገልግሎቶች።
የንግድ ድረ-ገጽ
በዲጂታል ዓለም ውስጥ እራስዎን የሚያሳይ፣ ደንበኞችን የሚስብልዎ፣ እና ስራዎን በሚገባው መልኩ የሚያቀርብ ድረ-ገጽ።
- ለንግድዎ የተሰሩ ገጾች — ልክ እንደ ፍላጎትዎ።
- ዲዛይኑ በሞባይልም ሆነ በኮምፒውተር በደንብ ይታያል — እንዲሁም ገጾቹ ሲከፈቱ በፍጥነት ይሰራሉ።
- ደንበኞችዎ እንዲያገኙዎት የሚያስችሉ የመገናኛ እና የጥያቄ ቅጾች ያካትታል።
- መሰረታዊ የኤስኢኦ ዝግጅት — ሰዎች በቀላሉ እንዲያገኙዎት።
ለንግድዎ የተሰራ ሲስተም
ከወረቀትና ከኤክሴል ተላቀቁ — በስራ ገበታዎ ሁሉንም ነገር በቀላሉ እንዲቆጣጠሩ የሚረዳ ስራዎ እንዴት እንደሚሄድ በመረዳት የተሰራ ሶፍትዌር።
- ቀጠሮ፣ እቃ ዝርዝር፣ ወይም ትዕዛዝ መቆጣጠሪያ — ሁሉም ስራዎ በሚሄድበት መንገድ የተበጀ
- ለሰራተኞች እና ለአስተዳዳሪዎች የተለየ የመዳረሻ መብት — እያንዳንዱ ሰው የሚሰራውን ብቻ እንዲመለከት የሚያስችል
- ወቅታዊ መረጃ እና ክትትል (ነገሮችን ወዴት እንዳሉ መቆጣጠርያ) — ሁኔታዎች እንዳሉ አሁን ባሉበት ሁኔታ ለማየት።
- አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆስቲንግ
ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና እንደአስፈላጊነታቸው ማሻሻያዎች
ሲስተምዎ ሁል ጊዜ እንዲሰራ፣ እንዲዘመን፣ እና እየተሻሻለ እንዲሄድ እንከታተላለን — አዲስ ሰው መቅጠር ሳያስፈልግዎ።
- ስህተቶችን ማስተካከል እና ትናንሽ ማሻሻያዎችን ማድረግ — ስራዎ ሁል ጊዜ እንዲሰራ እና እየተሻሻለ እንዲሄድ።
- ንግድዎ እየሰፋ ሲሄድ አዳዲስ ባህሪዎችን እንጨምርልዎታለን — ሲስተምዎ እንደ እርስዎ ፍጥነት ያድጋል።
- ማንኛውም ችግር ቢከሰት ለእርስዎ ቅድሚያ ሰጥተን እንመለሳለን — ስራዎ እንዳይቋረጥ ለማድረግ።
- በየወሩ ሲስተምዎ እንዴት እንደሚሰራ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እንፈትሻለን።
በኢንዱስትሪ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ ትብብር
ለዓመታት በሰሩበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ችግር ምን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ? ያንን እውቀትዎን ወደ እውነተኛ ሶፍትዌር እንለውጠው — እንደ አጋር እንጂ እንደ ተራ ደንበኛና አቅራቢ ሳይሆን በጋራ በመስራት።
- ሀሳብዎን ወደ ተጨባጭ የቴክኒክ እቅድ ለመቅረጽ የምናደርገው የመጀመሪያ ውይይት
- ከመንደፋችን በፊት ሀቀኛ የአዋጭነት እና የስራው መጠን ግምገማ
- ተለዋዋጭ የትብብር አማራጮች — ከክፍያ-ተኮር ግንባታ እስከ ረጅም ጊዜ አጋርነት ድረስ
- እርስዎ የኢንዱስትሪ እውቀቱን ያመጣሉ፣ እኔ ደግሞ ቴክኒካል ክህሎቱን አመጣለሁ
ምንም ያልተጠበቀ ነገር አይኖርም — ሁሉንም ነገር አስቀድመን እንነጋገራለን።
ስራ ከመጀመሩ በፊት ቋሚ ዋጋ ያገኛሉ — በሰዓት የሚቆጠር ግምት የለም። ለእያንዳንዱ ደረጃ የሚከፍሉት ስራውን ካዩ ካጸደቁ በኋላ ብቻ ነው። አቅጣጫው ትክክል ካልሆነ፣ ወደፊት ከመቀጠላችን በፊት አብረን እናስተካክላለን — እንጂ ስራው ከጨረስን በኋላ አይደለም።
እንዴት አብረን ልንሰራ እንችላለን?
ፕሮፖዛል
ስራው ምን እንደሚሸፍን፣ ደረጃ በደረጃ እንዴት እንደሚሰራ፣ እና እስከ መቼ እንደሚደርስ የሚገልጽ ዋጋ ያገኛሉ።
ግንባታ
ስራው እየተሰራ ባለበት ጊዜ ሁሉ፣ ስራው እንዴት እየሄደ እንዳለ በየጊዜው አሳውቅዎታለሁ — ስራው እይተሰራ እስከየት እንደደረሰ ለማየት የሚችሉበትን የሙከራ ማስፈንጠርያ(link) ይኖርዎታል።
ማስረከብ
ስራው ወደ ኦንላይን ይወጣል፣ ሙሉ ቁጥጥር ለእርስዎ ይሰጣል፣ እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ (በስምምነታችን በሚግለጽው የእይታ ጊዜ ቆይታ) የሚታዩ ስህተቶችን እናስተካክላለን።